ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ የፋና የህግ አማካሪ እና የትርጉም ድርጅት ሌላ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል – በዚህ ጊዜ በስዊድን የእዳ አስመላሽ ባለስልጣን (ክሮኖፎግደን) የቀረበ የተሳሳተ የይገባኛል ጥያቄ ላይ።
ለባለጉዳያችን፣ አደጋው ከፍተኛ ነበር። በአንድ የተሳሳተ ክስ ሰበብ የሚከተሉትን ነገሮች ሊያስከትል ይችል ነበር፡
- የክፍያ ውድቅ ማድረግ
- ለረጅም ዓመታት የሚቀጥል ገንዘብ ነክ ውስብስቦች
- ጭንቀት እና ስለመጻኢ እድል እርግጠኛ አለመሆን
- ቤት ለመከራየት፣ ብድር የማግኘት ወይም ሥራ የመቀጠር ያለውን እድል አስቸጋሪ ያደርገው ነበር።
እንደ አለመታደል ሆኖ፣ እንዲህ አይነት ጉዳዮች በጣም የበዙ ናቸው። ብዙ ግለሰቦች እና የንግድ ተቋሞች በተሳሳቱ፣ ቀነ ገደባቸው ያለፈ ወይም ሙሉ በሙሉ ፍትሃዊ ያልሆኑ የይገባኛል ክሶች ይቀርብባቸዋል። ተገቢ የህግ ድጋፍ ከሌለ፣ እነዚህ የይገባኛል ክሶች በፍጥነት ሊባባሱ ይችላሉ።
ጉዳዩ እንዴት እንደተከፈተ – በቅደም ተከተል
ደንበኛችን ሲያነጋግሩን፣ በጣም ተጨንቀው እና ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ተጋብተው ስነበር በፍጥነት ማደረግ የነበረንን እርምጃ ወስደናል፡
- ሙሉ የጉዳይ ግምገማ
እያንዳንዱን ሰነድ፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ ግንኙነት እና የህግ ዝርዝሮችን መርምረናል። - ስህተቶቹን መለየት
ይገባኛል ጥያቄው ህጋዊ መሰረት እንደሌለው እና የአሰራር ስህተቶችን እንደያዘ ደርሰንበታል። - የመግባቢያ ሂደቱን መቆጣጠር
ባለጉዳዩ አስጨናቂ ጥሪዎችን ወይም ደብዳቤዎችን በመቀበል እንዳይረበሹ ከከሳሹ ባለስልጣን ጋር የሚደረጉ ምልልሶችን ተቆጣጥረናል። - መደበኛ ተቃውሞ ማቅረብ
ትክክለኛ፣ ስህተቶቹን በግልጽ የሚያሳይ እና ህጉን የተከተል ተቃውሞ አዘጋጅን አቀረብን። - ጉዳዩ ተዘጋ — የደንበኛው ደህነንት ተጠበቀ
የእዳ አስመላሽ ባለስልጣን የይገባኛል ጥያቄውን ሙሉ በሙሉ አቆመ።
በእዳ ጥቁር መዝገብ ከመግባት ዳኑ። ከገንዘብ ኪሳራ እና ጭንቀት ተገላገሉ።
በምን ምክኛት አሸነፍን?
✔ ጥልቅ የህግ እውቀት
✔ ስለዝርዝር ጉዳዮች በሰጠነው ትኩረት
✔ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት
✔ ፈጣን እና ትክክለኛ እርምጃ
ይህ በዕድል የተገኘ ሳይሆን እውቀትን በአግባቡ በመጠቀማችን ነበር።
ይህ ለእርስዎ ምን ማለት ነው
ከየእዳ አስመላሽ ባለስልጣን ደብዳቤ ከደረሰዎት አይደናገጡ።
መፍትሄዎች አሉ – እና ስርዓቱን ብቻዎን መጋፈጥ የለብዎትም።
እኛ እንረዳዎታለን፡
- የተሳሳቱ የይገባኛል ጥያቄዎችን ይሟገቱ
- በተሰሳተ መንገድ ከእዳ አስመላሽ ባለስልጣን የቀረቡ እርምጃዎችን ያስቁሙ
- አግባብ የሌላቸው የክፍያ ስህተቶችን ያስወግዱ
- በእዳ ጥቁር መዝገብ እንዳይመዘገቡ ራስዎን ይጠብቁ
- የህይወትዎን አቅጣጫ መልሰው ይቆጣጠሩ
ስርዓቱ ከባድ በሚሆንበት ጊዜ ፋና ከእርስዎ ጎን ይቆማል።
👉 ዛሬውኑ ያግኙን
📧 fanajuridik.tolk@gmail.com
📲 +46 720‑254 320 | +46 762‑346 225

