በስዊድን ውስጥ የሚኖሩ ሰራተኞች በስራ አካባቢ ህግ (Work Environment Act)፣ በስራ ስምሪት ጥበቃ ህግ (LAS) እና በጋራ ውሳኔ አሰጣጥ ህግ (MBL)ን መሰረት ያደረጉ ጠንካራ የመብት ጥበቃዎች አሏቸው።
በስዊድን ውስጥ ያሉ ብዙ ሰራተኞች በአሰሪዎቻቸው የሚከተሉትን ነገሮች እንዲያደርጉ በሚያስገድዱ ሙከራዎች ምክንያት ጫና ይደርስባቸዋል፦
- በ”ያለፈቃድ/በቂ ምክንያት ከስራ መቅረት (olovlig frånvaro)” ማስፈራራት
- በፈቃደኝነት ስራቸውን እንዲለቁ መገፋፋት
- በተንኮል ወይም በማታለል ስራቸውን እንዲለቁ ማድረግ
- ለጤና ማገገሚያ (rehabilitation) ያለባቸውን ኃላፊነት አለመወጣት
- ስለሰራተኛ መብቶቻቸው የተሳሳተ መረጃ መስጠት
- በሐሰት ክሶች ማስፈራራት
እናም መብታቸውን ለማስጠበቅ የተቋቋመው የሰራተኛ ማህበራቸው ድጋፍ ከመስጠት ሲቆጠብ ወይም ሲያንገራግር ሰራተኞቹ አውላላ ሜዳ ላይ ብቻቸውን እንደቀሩ ይሰማቸዋል።
ነገር ግን የስዊድን የሰራተኞች ህግ ለሰራተኞች ጠንካራ ጥበቃ ይሰጣል — እናም እነዚህን መብትዎችን ማወቅ ያዎታል።
🔥 አሰሪዎች የሰራተኞቻቸውን መብቶች ለመሸራረፍ የሚጠቀሙባቸው የተለመዱ ዘዴዎች
✔ በ”ያለፈቃድ ከስራ መቅረት” ማስፈራራት
ብዙውን ጊዜ ለማስፈራራት ጥቅም ላይ ይውላል — ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ህገ-ወጥ ነው።
✔ ”ለእርስዎ የሚሆን የስራ ቦታ የለንም”
ህጋዊ ምክንያት ሳይኖር፣ ከህመም እረፍት በኋላ ወደ ስራ ሲመለሱ አሰሪዎች መመለስዎን ሊከለክሉ አይችሉም።
✔ ”ስራ ቢለቁ ይሻላል”
ይህ ህጋዊ ግዴታዎችን ለማምለጥ የሚደረግ የማታለል ሙከራ ነው።
✔ ”ስራ እየፈለጉ እያለ ክፍያ አንሰጥዎትም”
ለስራ ዝግጁ እስከሆኑ ድረስ፣ ስራ ሳይሰሩም ደመወዝ የማግኘት መብት (tjänstledig) ሊኖርዎት ይችላል።
✔ ድጋፍ የማይሰጡ የሰራተኞች ማህበራት
አንዳንድ ማህበራት እርምጃ ባለመውሰዳቸው ሰራተኞች ያለ ጥበቃ ይቀራሉ።
🧠 መብቶችዎን ይወቁ

📌 LAS – የስራ ጥበቃ ህግ (Employment Protection Act)
የሚከተሉት መብቶች አሉዎት፦
- ስራዎን እንዲለቁ ከተጠየቁ ውሳኔው ላይ ተጨባጭ ምክንያቶች መኖር አለባቸው
- ስራ ከማቋረጥዎ በፊት ወደ ሌላ ስራ የመዛወር እድል አለዎ
- ከአሰሪዎ በጽሁፍ የሚሰጥ ማሳወቂያ ሊደርስዎ ይገባል
- በሰራተኛ ማህበርዎ አማክይነት ከአሰሪዎ ጋር ድርድር የማድረግ መብት
📌 የስራ አካባቢ ህግ (Arbetsmiljölagen)
አሰሪዎች የሚከተሉትን ማድረግ አለባቸው፦
- በስራ ቦታ ላይ በሰራተኞች ላይ የጤና ችግሮችን የሚያስከትሉ ነገሮች መከላከል
- የስራ አካባቢውን የእያንዳንዱን ሰራተኛ ፍላጎት ያከተቱ ምቹ ሁኔታዎችን ማስተካከል
- የስራተኞቻቸው ጤና በአደጋ ወይም በሌላ ጉዳይ ለጤና ማገገሚያ (rehabilitation) ድጋፍ መስጠት
📌 MBL – የጋራ ውሳኔ አሰጣጥ ህግ (Co-Determination Act)
የሚከተሉት መብቶች አሉዎት፦
- ከቀጣሪዎ ጋር ድርድር የማድረግ
- በጠበቃ ወይንም በስራተኛ ማህበርዎ ውክልና የማግኘት
- ጉዳይዎን በተመለከት ግልጽ እና ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት
📌 የሰራተኛ መብቶችን በተመለከተ ሃላፊነት የተሰጣቸው መንግስታዊ አካላት
- የስዊድን የስራ አካባቢ ባለስልጣን (Arbetsmiljöverket)
https://www.av.se
- የስራ ጉዳዮች ፍርድ ቤት (Arbetsdomstolen)
https://www.arbetsdomstolen.se
- የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ (Försäkringskassan)
https://www.forsakringskassan.se
- የእኩልነት እምባጠባቂ (Diskrimineringsombudsmanne – DO)
https://www.do.se
🤝 Fana እንዴት ድጋፍ ይሰጥዎታል
✔ የአሰሪዎችን ማስፈራሪያ እንገመግማለን
✔ ህጋዊ መብቶችዎን እናብራራለን
✔ በሙያዊ መንገድ ምላሽ እንዲሰጡ እንረዳዎታለን
✔ ከሰራተኛ ማህበርዎ (Facket) ጋር ስብሰባዎችን እናመቻቸለን
✔ ሁሉንም ነገር በሰነድ እንዲይዙ እንረዳለን
✔ቀጣሪዎ አለአግባብ ከስራ እንዲለቁ ካስገደድዎ ክስ እንዲመሰረቱ እንደግፋለን
✔ ይግባኝ እና ቅሬታ በማቅረብ ሂደት እንረዳለን
ከአሰሪ ጋር በሚፈጠር አለመግባባት ላይ ብቻዎን መታገል የለብዎትም።
📣 ከአሰሪዎ ጋር አለመግባባት አለብዎት? ነገር ግን የሰራተኛ ማህበርዎ (Facket) ድጋፍ ለመስጠት እያንገራገረ ነው?
👉 መብቶች እንዳለዎትና ማስከበር እንዲሚችሉ አይዘንጉ።
👉 መብትዎን ለማስከበር ፋናን ዛሬውኑ ያግኙ።

