ማዘጋጃ ቤቱ (ኮምዩን) እና የማህበራዊ ዋስትና ተቋሙ (ፎርሽክሪንግካሳ) ሃላፊነት ላለመወጣት ጣት ሲጠቋቀሙ እርስዎ ያለ ድጋፍ ከቀሩ፡ መብትዎን ይወቁ! 

ማዘጋጃ ቤቱ (ኮምዩን) እና የማህበራዊ ዋስትና ተቋሙ (ፎርሽክሪንግካሳ) ሃላፊነት ላለመወጣት ጣት ሲጠቋቀሙ እርስዎ ያለ ድጋፍ ከቀሩ፡ መብትዎን ይወቁ!  - 1

አማርኛ

ኦቲዝም፣ ኤዲኤችዲ ወይም ሌሎች የአካልና የአእምሮ አሠራር ልዩነቶች (functional variations) ያላቸው ልጆች ወላጆች እንዲሁም የአካል ጉዳት ያለባቸው አዋቂዎች፣ በደህንነት እና በክብር ለመኖር የሰው ድጋፍ (personal assistance) ለማግኘት ማመልከቻ ለሚመለከተው ባለስልጣን መ/ቤት ያስገባሉ።

ነገር ግን ብዙ ጊዜ ውድቅ ይደረግባቸዋል፤ ለዚህ ምክንያት ከሆኑት ጉዳዮች መሃከል ባለስልጣን መ/ቤቶች ኃላፊነታቸውን ላለመወጣት «ይህ የማዘጋጃ ቤቱ ኃላፊነት ነው።» «ይህ የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲው ኃላፊነት ነው።» እርስ በርስ ጣት ይጠቆቋማሉ፡- አልያም 

«መስፈርቶቹን አያሟሉም።» ወይንም “ይህ እንደ መሰረታዊ ፍላጎት አይቆጠርም።” በሚሉ ምክንያቶች ማመልከቻዎ ውድቅ ይደረጋሉ። 

ውጤቱስ?

ድጋፍ የማግኘት መብት ያላቸው ሰዎች ያለ ድጋፍ ይቀራሉ።

🔍 ይህ ለምን ይከሰታል?

✔ የግል ድጋፍ አገልግሎት ውድ በመሆኑ ወጪን ለመቀነስ እንዲሁም ሁለቱም ተቋማት ኃላፊነቱን ለመሸሽ ይሞክራሉ።

የተሳሳቱ ግምገማዎች 

አብዛኛዎቹ የጉዳይ ኃላፊዎች (caseworkers) ስለ ነርቭ-እድገት ሁኔታዎች (neurodevelopmental conditions) በቂ እውቀት የላቸውም።

ግልጽ ያልሆነ የኃላፊነት ክፍፍል

በዚህም ምክንያት ቤተሰቦች በሁለት ባለሥልጣናት መካከል ባለው እሰጥ አገባ አጣብቂኝ ውስጥ ይገባሉ።

የሰነድ ጉድለት

ብዙ ማመልከቻዎች ውድ የሚደረጉት ሰነዶቹ ያልተሟሉ ወይም በተሳሳተ መንገድ የተሞሉ በመሆናቸው ብቻ ነው።

ማዘጋጃ ቤቱ (ኮምዩን) እና የማህበራዊ ዋስትና ተቋሙ (ፎርሽክሪንግካሳ) ሃላፊነት ላለመወጣት ጣት ሲጠቋቀሙ እርስዎ ያለ ድጋፍ ከቀሩ፡ መብትዎን ይወቁ!  - 3

🧠 መብቶችዎን ማወቅ ያለብዎት ለምንድን ነው?

በስዊድን ህግ (LSS እና የማህበራዊ ዋስትና ህግ) መሰረት፣ በሚከተሉት ሁኔታዎች ድጋፍ የማግኘት መብት አለዎት፦

✔ሰፊ የሆነ የዕለት ተዕለት ፍላጎቶች ሲኖሩዎት

✔ለመሠረታዊ ፍላጎቶችዎ እርዳታ ሲያስፈልግዎ

✔ዕለት ተዕለት ኑሮዎን የሚነካ የአካል ወይም የአእምሮ እክል ሲኖርዎት

✔ልጅዎ የአእምሮ እና/ወይም የአካል እድገት ተግዳሮቶች ካለባት/በት

✔እንዲሁም የሚከተሉት መብቶች አሉዎት፦

✔በጉድይዎ ላይ ትክክለኛ የሆነ የምርመራ ሂደት የማግኘት

✔ህጋዊ ውሳኔ የማግኘት

✔ውሳኔው ውድቅ ከተደረገ ይግባኝ የመጠየቅ

✔ተጨማሪ ማስረጃዎችን የማቅረብ

✔ውሳኔው የተሳሳተ ከሆነ ክርክርዎን የማሸነፍ

🛡️የተሳሳተ ውድቅ ውሳኔን በጭራሽ አይቀበሉ!

ብዙ ውድቅ የተደረጉ ጉዳዮች ስህተት ያለባቸው ናቸው፤ እንዲሁም ውሳኔዎቹ ሊቀየሩ ይችላሉ።

እርስዎም የሚከተሉትን እርምጃዎች በመውሰድ ውሳኔውን ሊያስቀይሩ ይችላሉ፦

✔ይግባኝ በመጠይቅ

✔ትክክለኛ ሰነዶችን ሲያቀርቡ

✔የባለሙያ እርዳታ ሲያገኙ

✔ፍላጎቶቻቸውን በግልጽ ሲያሳዩ

🤝 ፋና በምን መልኩ ይደግፍዎታል?

ማዘጋጃ ቤቱ (ኮምዩን) እና የማህበራዊ ዋስትና ተቋሙ (ፎርሽክሪንግካሳ) ሃላፊነት ላለመወጣት ጣት ሲጠቋቀሙ እርስዎ ያለ ድጋፍ ከቀሩ፡ መብትዎን ይወቁ!  - 5

✔ ማመልከቻ በመጻፍ

ጠንካራ እና በህግ ላይ የተመሰረተ ማመልከቻ እንዲያዘጋጁ እንረዳዎታለን።

✔ ሰነዶች

ምን ዓይነት ሰነዶች እና የህክምና ማስረጃዎች እንደሚያስፈልጉዎ መመሪያ እንሰጥዎታለን።

✔ ግንኙነት

ከማዘጋጃ ቤቱ (ኮምዩን) ወይም ከማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ (ፎርሽክሪንግካሳ) ጋር እንዲገናኙ ሁኔታዎችን እናመቻቻለን።

✔ ውድቅ የተደረጉ ማመልከቻዎች

ውሳኔውን እንመረምራለን እንዲሁም ችግሩ ምን እንደነበር እናብራራለን።

✔ ይግባኝ

የህግ መስፈርቶችን የሚያሟላ እና በሙያዊ ደረጃ የተዘጋጀ የይግባኝ ማመልከቻ እናዘጋጃለን።

✔ የቋንቋ ድጋፍ

በአማርኛ፣ በትግርኛ በእንግሊዝኛ፣ በስዊድንኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች አገልግሎት እንሰጣለን።

የግል ድጋፍ ተከልክለዋል?

👉 መብቶች አሉዎት።

👉 ክርክርዎን ማሸነፍ ይችላሉ።

👉 ብቻዎን መታገል አይጠበቅብዎትም።

📞 ዛሬውኑ ፋናን ያግኙ — ሁልጊዜም ከጎንዎ ነን።