ከተጣማውሪዎ፣ ከልጅዎ ወይም ከሌላ ዘመድዎ ጋር በስዊድን ለመኖር የመኖሪያ ፈቃድ ሲያመለክቱ፣ የስደተኞች መስሪያ ቤት ባልስልጣን ግልጽ የሆነ ሂደት ይከተላል። ቀላል ዝርዝር መግለጫው ይሄን ሲመስል ፋና በእያንዳንዱ ደረጃ በዚህ መልኩ ያግዝዎታል።
🧩 1. ማመልከቻዎን ያስገቡ
ማመልከቻውን ሰነዶች ከሰነድችዎ ጋር በማያያዝ ካስገቡ በኋል ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ኤምባሲውን ይምረጡ።
👶 ማመልከቻው ልጅዎን የሚመለከት ከሆነ
ወላጅ ወይም ህጋዊ አሳዳጊ ማመልከቻውን ማስገባት አለበት።
2. በስዊድን ውስጥ የሚኖረው አመልካች መጠይቅ የሚያደርግ ሲሆን
ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ መስጠት አለብዎ፡
- ስለ ወር ገቢዎ
- ስለ መኖሪያ ቤታዎ
- አብርዎት ለመኖር ከሚመጣው ግለሰብ ጋር ያለዎ ግንኙነት
መጠይቁን በ14 ቀናት ውስጥ ሞልተው ለስደተኞች መ/ቤት ማስረከብ አለብዎ።
📝3. የቃለ መጠይቅ ቀጠሮ ካሲያዙ በኋላ ፓስፖርትዎን ያሳያሉ
ከመረጡት ኢምባሲው ውስጥ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ቀጠሮ እንዲያስይዙ የሚጠይቅ ኢሜይል ወይም ደብዳቤ ይደርስዎታል። ከዛም፡
- ፓስፖርትዎን
- ሁሉንም ሰነዶች
በመያዝ ወደ ኤምባሲው በመሄድ አብርዎት ለመኖር ከሚመጣው ግለሰብ ጋር ስላለዎ ግንኙነት ጥያቄዎች ይቀርብልዎታል። ቪዛ ከፈለጉ፣ ለወደፊት የመኖሪያ ፈቃድ ካርድዎ የሚሆን የጣት አሻራዎን በመስጠት ፎቶ ይነሳሉ።
4. የፍልሰት መስሪያ ቤት ባልስልጣን ጉዳይዎን ይመረምራል
ሁሉንም መረጃዎችዎን ከገመገመ በኋላ፡
- ተጨማሪ ዝርዝሮችን ሊጠይቅ ይችላል
- በስዊድን የሚኖረውን አመልካች ሊያነጋግሩ ይችላል።
- መስፈርቶቹ ካልተሟሉ ወዲያውኑ ማመልከቻውን ውድቅ ሊያደርጉ ይችላሉ
📬 5. ውሳኔ ይደርስዎታል
ማመልከቻዎን በበይነመረብ ላይ ካስገቡ፣ ውሳኔው ዝግጁ ሲሆን ኢሜይል የሚደርስዎት ሲሆን ውሳኔው ወደ ኤምባሲው ወይምን ወደ ተወካይዎ ይላካል።ቅጂው በስዊድን ላለው ሰውም ይላካል። ማመልክቻዎ ተቀባይነት ካገኘ ስዊድን ውስጥ ለመኖር እና ለመስራት ይችላሉ። ማመልክቻዎ ደግሞ ውድቅ ከተደረገ ጓዝዎን ጠቅለው ስዊድንን ለመልቀቅ መዘጋጀት አለብዎት።
👶ስዊድን ውስጥ ለተወለዱ ልጆች የሚጠየቅ ማመልከቻ
- በስዊድን ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ ያለው ወላጅ ማመልከቻውን ያስገባል
- የልጅዎን ፓስፖርት ማሳየት አለብዎ
- ለመኖሪያ ፈቃድ ካርድ እንዲያገለግል ልጁ/ልጅቷ ፎቶግራፍ ይነሳል/ትነሳለች
- በመጨረሻም ውሳኔው ወደ ወላጅ ወይም አሳዳጊ አድራሻ ይላካል።
👧የማደጎ ልጆችን በተመለከት
- አሳዳጊ ወላጅ ማመልከቻውን ያቀርባል
- የልጁ/ልጅቷ ፓስፖርት ኤምባሲው ጋር መቅረብ አለበት
- ከ5 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች በኤምበሲው መገኘት አለባቸው
- ቪዛ የሚያስፈልጋቸው ልጆች የጣት አሻራ መስጠት እና ፎቶ መነሳት አለባቸው።
🤝ፋና በምን መልኩ እንደሚደግፍዎት
✔ ማመልከቻውን በተመለከተ ግልጽ መመሪያ
✔ የሰነድ ዝግጅት
✔ ትርጉም
✔ ለቃለ መጠይቅ ዝግጅት
✔ በቃለ መጠይቁ ላይ እገዛ
✔ የውሳኔ ማብራሪያ
✔ የይግባኝ ድጋፍ
በማመልከቻዎ ዙሪያ እገዛ ይፈልጋሉ?
📞 እንግዲያውስ ፋናን ያግኙ – ከጅምሩ እስከፍጻሜው እንደግፍዎታለን።

