በስዊድን የቤተሰብ ውህደትን በተመለከተ የተጠቆሙ ጥብቅ የህግ ረቂቆች!

በስዊድን የቤተሰብ ውህደትን በተመለከተ የተጠቆሙ ጥብቅ የህግ ረቂቆች! - 1

አማርኛ

በስዊድን የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ቤተሰቦቻቸውን ለማስመጣት ከፈለጉ ገቢያቸው ከቀድሞው መስፈርት በ30% ይጨምራል

አዲሱ ረቂቅ ህግ ከጥር 1 ቀን 2027 ጀምሮ ተግባራዊ ከሆነ፣ ማንም ሰው ቤተሰቡን ወደ ስዊድን ማምጣት የሚፈልግ ከሆነ፣ በስዊድን የነበረው የቤተሰብ አባል ከግብር በኋላ 23,818 ክሮኖር መክፈል አለበት። ይህ ማለት የራስን መቻል ሂደት መለኪያ ከቀድሞው አሰራር በ30 በመቶ ይጨምራል ማለት ነው።

በስዊድን የቤተሰብ ውህደትን በተመለከተ የተጠቆሙ ጥብቅ የህግ ረቂቆች! - 3

አዲሱ ረቂቅ ህግ ተግባራዊ ከሆነ፣ ለትምህርት ወደ ስዊድን የሚመጡ ተማሪዎች በቤተሰብ ውህደት ምክንያት የትዳር አጋራቸውን ወይም ልጃቸውን ወደ ስዊድን ማምጣት አይችሉም።

ከዚህም በተጨማሪ፣ ከአውሮፓ ህብረት እና ከስካንዲኔቪያ ውጭ ያሉ ብዙ ስደተኞች፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነ ያገኙት  እንኳን፣ ቤተሰቦቻቸውን ወደ ስዊድን ለማምጣት ከፈለጉ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት በስዊድን መኖር አለባቸው። በዚህ በወጣው ረቄቅ መሰረት ስራ በመስራት ከሚገኙ ገቢዎቻ ማለትም ከማህበራዊ ድጎማ (A-kassa) ወይም ከሌሎች የመንግስት ድርጅቶች የሚሰጡ ገንዘባዊ ድጋፎች እንደ የገቢ መለኪያ አይቆጥርም።

ሆኖም፣ ረቂቅ ህጉ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ይህ በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ቤት የገቡ ቤተሰቦች ቤተሰቦቻቸውን እንደገና እንዲያሰባስቡ ትልቅ እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ።

የስዊድን መንግሥት አዲስ ረቂቅ ሕግ ተግባራዊ ከሆነ በጥር 1 ቀን 2027 ዓ.ም. እንደሚጀመር ታቅዷል። ሆኖም ግን፣ ረቂቅ ሕጉ ሕግ ከመሆኑ በፊት ለስዊድን ፓርላማ ቀርቦ መጽደቅ አለበት።

ምንጭ ቲቲ የዜና አገልግሎት

ቁልፍ ቃላት፡ የቤተሰብ ውህደት፤ ፍልሰትኞች፤ ስዊድን፤ ስደተኛ

መስከረም የሺአረጋ ካሳ