ስዊድን አገር ውስጥ ያለውን የፍልሰት ሂደት ለመገንዘብ ከባድ ሊሆን ይችላል። በፋና ህግ አማካሪና የትርጉም አገልግሎት ደርጅት፣ በፍልሰት ህግ ዙሪያ የህግ እውቀትን ከባለሙያ አስተርጓሚዎች ጋር ስለምናጣምር ጉዳይዎን በግልጽ እና ትክክለኛ መንገድ ለማቅረብ ድጋፍ ይሰጥዎታል።
🛂 ፋና የሚክከተሉትን ማመልከቻዎች ለመንግስታዊ መስሪያቤቶች ለመላክ ያግዝዎታል፡
- የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻዎች
- የመኖሪያ ፈቃድ ማራዘሚያዎች
- የዜግነት ጥያዌ ማመልከቻዎች
- ለቤተሰብ ውህደት እና የቤተሰብ አባላትን ከአገር ቤት ወይም ከሌላ ሶስተኛ አገር ለማስመጣት ማመልከቻ ለመጻፍ
- ከፍልሰት መ/ቤቱ የሚቀርቡ አቤቱታዎች እና ውሳኔዎች ላይ ይግባኝ
የእያንዳንዱ ግለሰብ ጉዳይ ከሌላው ጋር ልዩነት እንዳለው ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጉዳይዎን በአክብሮት፣ ተቀብለን በትክክለኛ እና ማስተዋል በተሞላበት መንገድ እንቀርባለን።
🗣️ በፍልሰት ጉዳዮች ላይ ትርጉም ያለው ወሳኝ ሚና
ከባለስልጣናት ጋር ሲነጋገሩ እያንዳንዱ ዝርዝር ጉዳይ ዋጋ እንዳለው ስለሚገነዘቡ አስተርጓሚዎቻችን የሚከተሉት መሰረታዊ ጉዳይዎች መሟላታቸውን ያረጋግጣሉ፡
- ሁሉንም ሰነዶችዎን እና ውሳኔዎችን በትክክል እንዲረዱ
- ጉዳይዎን በራስ መተማመን ለመግለጽ እንዲችሉ
- እያንዳንዱ ዝርዝር ጉዳይ እንዳይረሳ እና በትክክለኛው መንገድ እንዲቀርብ
- ሂደቱ ግልጽ እና ህጉን በተከተለ መንገድ እንዲካሄድ
- ትክክለኛ ትርጓሜ ለወደፊቱዎ ኢንቨስትመንት ነው።
⚖️ በጉዳይዎ ላይ ለውጥ የሚያመጣ የህግ እውቀት
ፋናን ከሌሎች መሰል ድርጅቶች የሚለየው፡
- እያንዳንዱን ባለጉዳይ ያካተተ ህጋዊ ድጋፍ በመስጠቱ
- ጉዳይዎ እንዲሳካ ስልታዊ እቅድ ስለሚያወጣ
- በሰነዶች እና በማስረጃዎች ድጋፍ ስለሚሰጥ
- ከቀጠሮዎ በፊት ቅድመ ድጋፍ
ግባችን አስጨናቂውን የፍልሰት ሂደት በግልጽነት እና በራስ መተማመን ማሳካት እንደሚቻል ማስመስከር ነው!
📍 ይጎብኙን
ዳንማርክስጋታን 19፣ ሺስታ
ከህዝብ ማመላለሻ አገልግሎቶች አጠገብ ስለሆነ ወደ ጽ/ቤታችን ለመምጣት ቀላል ነው። ሺስታ ምድር ባቡር ጣቢያው አጠገብ።
📲 ያግኙን
+46 720 254 320
+46 762 346 225
ኢሜይል FanaJuridik.Tolk@gmail.com
📞 ነፃ ምክክርዎን ያስይዙ
በስደት ጉዳይ ላይ እርዳታ ይፈልጋሉ?
👉 ዛሬ ያግኙን – በእያንዳንዱ እርምጃ ከእርስዎ ጋር ነን።

